
የወጪ ንግዱን ለማሳለጥ ለላኪዎች ቅዳሜና እና እሁድ ጭምር አገልግሎት ይሰጣል
የወጪ ንግዱን ለማሳለጥ ለላኪዎች ቅዳሜና እና እሁድ ጭምር አገልግሎት ይሰጣል =================================== አዲስ አበባ 14/2/2017(ንቀትሚ)ለላኪዎች አስፈላጊውን መንግስታዊ አገልግሎት በመስጠት የወጪ ንግድ ስራን ምቹና ውጤታማ ለማድረግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የቅዳሜ እና አሁድ አገልግሎት እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር ገለጹ፡፡ የሀገራችንን የወጪ ንግድ ካሉበት ችግሮች በማላቀቅ ለሀገርም ሆነ ለላኪዎች አዋጪ እንዲሆን ለማስቻል የተለያዩ የአሰራር እና የግብይት ስርዓቶች እየተዘረጉ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ የወጪ ንግድን በበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማቱ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስረድተዋል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የወጪ ንግድ አፈፃጸም እና በቅባት እህሎች እና የጥራጥሬ ምርቶች የቀጥታ ግብይት ሥርዓት መመሪያ ላይ ከላኪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱም በሩብ ዓመቱ ከባለፈው ዓመት ብልጫ ያለው አፈፃጸም መመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን ላኪዎች መመሪያውን በመረዳት ወደ ተግባር እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡